የሰላሌ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች
መደበኛና ማታ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 54 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል ።
ዩኒቨርስቲው በ3ኛ ዙር ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 428 ተማሪዎች ሴቶች ናቸው።
የዩኒቨርስቲው ኘሬዜዳንት ዶክተር ገናነው ጎፌ ሰላሌ ዩኒቨርስቲ ለትምህርት ጥራት ሰጥቶ ብቃትና ክህሎት ያላቸው ተማሪዎችን በማፍራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።ዩኒቨርስቲው ትምህርት የሚሰጥባቸውን ፕሮግራሞች 34 ማድረሱንም ገልጸዋል ።የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።ተመራቂ ተማሪዎች ሀገራቸው ከችግር ተላቃ በእድገት ጎዳና እንድትራመድ በማድረግ የቀሰሙትን እውቀትና ልምድ ወደ ተግባር ሊቀይሩ ይገባል ብለዋል።ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሀገሪቱ የሚታዩ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ብልጽግና እንዲመጣ ከፍተኛ ኋላፊነት መወጣት አለባቸው ብለዋል።ማህበራዊ ትስስር እንዲላላ ባለፋት 27 አመታት መሰራቱን የገለጹት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ህብረብሔራዊ አንድነት እንዲመጣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትልቅ ሚና ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።