• photo_2022-02-02_15-05-53.jpg
  • 1H7A1574.JPG
  • F6.jpg
  • F10.jpg
  • F3.jpg
  • 1H7A5386.JPG
  • Library.JPG
  • F8.jpg
  • F9.jpg
  • photo_2022-02-02_15-05-54.jpg
  • fard.jpg
  • F5.jpg
  • 1H7A5756.JPG
  • photo_2022-02-02_15-06-15.jpg
  • 1H7A1721.JPG
  • 1H7A5279.JPG
  • meeting.jpg
  • F7.jpg
  • 1H7A5644.jpg
  • photo_2022-02-02_15-06-13.jpg
  • Sport .jpg
  • 1H7A5189.JPG
  • 1H7A8882.JPG
  • _H7A4385.JPG
  • Cafeteria.jpg

Who's Online

We have 84 guests and no members online

Announcements

  Vacancy

  Bids

በሰላሌ ኦሮሞ ባህል ማዕከል የተሰጠውን የሶስት ቀን ስልጠና ያዘገጀው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ህጻናት፤ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ሲሆን በስልጠናው የተሳተፉት ደግሞ ከተለያዩ የአስተዳደር ከፍሎች የተውጣጡ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሴት

የአስተዳደር ሰራተኞችና አካል ጉዳተኞች ናቸው፡፡ ስልጠናውም የተሰጠው ከኢትዮጲያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በመጡ አሰልጣኞች ነው፡፡

በስልጠናው ፕሮግራም ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገናነው ጎፌ እንደተናገሩት የአገልግሎት አሰጣጣችንን ከግዜ ወደ ጊዜ በማሻሻልና በማዘመን ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ እነዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ግብ ለማሳካት ስልጠናው ጉልህ አስተዋጽዖ አለው በማለት ስልጠናውን እስከ መጨረሻው በትጋትና በንቃት እዲከታተሉ ለሰልጣኞቹ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ስልጠናው በዋናነት ያተኮረው በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ስነ ምግባር ዙሪያ፣ የመልካም አስተዳደር መሰረታዊ መርሆች ፣ከአገልጋይ ሰራተኛ ምን ይጠበቃልና ወዘተ የመሳሰሉትን ዋና ዋና ርዕሶች ላይ ነበር፡፡ ለሶስቱም ቀናት በነረው የስልጠና መረሃ ግብር ሰልጣኞቹ በሁለት ምድብ ተከፍለው የሰለጠኑ ሲሆን ሰፊ ውይይትና ምክክር አካሂደዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት በሁለቱም የስልጠና ታዳሚዎች ዘንድ የተነሱትን ሃሳብ አሰተያየትና ጥያቄዎች በአሰልጣኞቹ አማካኝነት ቀርቦ በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በመምህርት ሃና ታምራት ማጠቃለያ ተሰጥቶበታል፡፡

በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት አቶ አዱኛ መኮንን በስልጠናው መዝግያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር በስልጠናው ያገኘነውን እውቀተና ከህሎት ይበልጥ በማጎልበት የአገልግሎት አሰጣጣችንን በማዘመን ሁላችንም ባለንበት የስራ ክፍል የበኩላችንን ሃላፊነት ከተወጣን ዩኒቨርሲቲውን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ እንችላለን በማለት ም/ፕሬዝዳንቱ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመቀጠልም ም/ፕሬዝደንቱ፤ የዩነቨርሲቲው ሴት አስተዳደር ሰራተኞች ስልጠናውን በላቀ ምግባር በመከታተል እንዲሁም ገንቢ ሃሳብ፤ አስተያየትና ጥያቄዎቻቸውን በሰለጠነ መንገድ በማቅረብ ላሳዩት መልካም አርኣያነት ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና ችረዋል፡፡

በመጨረሻም አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎች እንደተናገሩት በተሰጣቸው ስልጠና የተደሰቱ መሆኑን ገልጸው፤ ስለ ለደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ መሰረታዊ መርሆችና ለአገልግሎቱ ብቁ የሚያደርጉ ነገሮች ላይ ያላቸውን የግንዘቤ ክፍተቶች ያሟላላቸው በመሆኑና በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎቶች ወደ ተግባር በመቀየር የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ እንዴት ማገልገል እንደሚቻል ብዙ ግንዛቤ ማገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

 

Visitors Counter

963357
TodayToday2480
YesterdayYesterday2948
This_WeekThis_Week15854
This_MonthThis_Month2480
All_DaysAll_Days963357

 Partnerships

Oromia Health Bureau

Ethiopian Biodiversity Institute

Oromo Research and Cultural  Development Center Ethiopian Radiation Protection Authority Books for Africa