Who's Online

We have 130 guests and no members online

Announcements

  Vacancy

  Bids

Online exam platform

    

                           የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት                                                                                                    

 የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 15/2009 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን እንደማንኛዉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት/ ዩኒቨርሲቲዎች ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በአዋጅ ቁጥር 359/2008 ሲቋቋም በህግ አገልግሎት ክፍል በመዋቀር የተለያዩ የህግ ነክ ሥራዎችን ሲያከናዉን በመቆየት በአዲሱ የሥራ ምዘናና የነጥብ አሰጣጥ ዘዴ እንደ ዩኒቨርሲቲያችን አዲስ መዋቅር ሲሰራ መጋቢት 01/2010 ዓ.ም በዳይሬክቶሬት የሥራ ደረጃ በማደግ እንዲሁም ዳይሬክተር እና ከፍተኛ ባለሙያ ተመድቦለት በዳይሬክቶሬት ደረጃ መደበኛ ሥራዉን ጀምሯል፡፡ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከሚያከናዉናቸዉ ተግባራት ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተሉት ቀርበዋል፡-

  • ልዩ ልዩ ህገ ነክ ጉዳዮችን መተንተን፤ መተርጎምና ለፖሊስ ዉሳኔዎች የመሰረተ ሀሳብ ማቅረብ፤
  • በህግ ነክ ጉዳዩች ላይ፤ መሥርያ ቤቱ የሚያደርገዉን ድርድርና ስምምነት ዉጤታማ በማድረግ ረገድ እንዲሁም የመሥሪያ ቤቱን ጥቅም ማስከበርና የህግ ግንዛቤ ክፍተቶችን ማሟላት፤
  • በአፈፃፀም ላይ ክፍተት ያለባቸዉ ስራዎችን በመለየት ማብራሪያና አስተያየት የመስጠት ስራ መስራት፤
  • መሥሪያ ቤቱ ከሌላ ወገን ጋር በሚያደርገዉ የድርድር ነጥቦች ላይ ስምምነት የተደረሰባቸዉንና ልዩነት የታየባቸዉን ጉዳዮች መለየት፤ የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ከህግ አኳያ በመመርመር የዉሳኔ ሃሳብ ለበላይ አመራሩ የማቅረብ ሥራዎችን መስራት፤
  • የተለያዩ የዉል ስምምነቶችን የማዘጋጀት፤
  • በዩኒቨርሲቲዉ (በተቋሙ)ላይ ለሚቀርቡ ማንኛዉም ክሶች ተቋሙን (ዩኒቨርሰቲዉን) በመወከል መልስ የመስጠት ሥራ መስራት፤
  • መሥሪያ ቤቱን ወክሎ መልስ በማዘጋጀት መከራከር፤ ይግባኝ መጠየቅ፤ የፍርድ አፈፃፀሙን የመከታተል ሥራ መስራት፤
  • ዉስብስብነት ባላቸዉ የህግ ነክ ጉዳዮች ላይ ለመሥሪያ ቤቱ የሥራ ክፍሎች የምክር አገልግሎት መስጠት፡፡
  • በዩኒቨርሲቲዉ የሚገኙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ህጎችን፣ መመሪያዎችንና ደንቦችን በመገንዘብ ተግባራቸዉን ህግንና ህግን ብቻ ተከትለዉ እንዲያከናዉኑ ለማስቻል የተለያዩ የሀገሪቱን ህጎች ፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን እንዲጠቀሙበት የማመቻቸትና የማማከር ሰፊ ሥራ መስራት፤
  • ዩኒቨርሰቲዉ (ተቋሙ)አዲስ ከመሆኑ አንፃር የአሰተዳደር ሰራተኞችም ሆነ የተቋሙ መምህራን የሚዳኙበት እንዲሁም ቅሬታቸዉን የሚያቀርቡበት የዲሲፕሊን ኮሚቴና የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እንዲቋቋም አወጁንና ደንቡን መሰረት በማድረግ ለዩኒቨርሰቲዉ የበላይ አካል የዉሳኔ ሃሣብ ማቅረብ፤
  • በፍትሐ ብሄር ጉዳዮች ላይ የሚፈጸሙ የሕግ እና ዉል ጥሰቶችን በመለየት በመደበኛ ፍርድ ቤቶች በማቅረብ የተቋሙን/ የዩኒቨርሲቲዉን ጥቅም ማስጠበቅ፤
  • በመደበኛ ፍርድ ቤቶች እና በአስተዳደር ፍርድ ቤት የተወሰኑ ዉሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፤
  • ዩኒቨርሲቲዉ ከተለያዩ አካላት ጋር የሚገባቸዉ ዉሎች ለበላይ አመራሩ ቀርበዉ ከመጽደቃቸዉ በፊት በአግባቡ መዘጋጀታቸዉን የማረጋገጥ ሥራዎችን መስራት፤
  • የተለያዩ የሀገሪቱ ህጎች፣ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የዩኒቨርሲቲዉ ሴኔት ሌጂስሌሽን በሥራ ላይ መዋላቸዉን መከታተል፤
  • በመንግስት ንብረት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መከታተል፤
  • ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ላይ ብርቱ ክትትል ማድረግ፤
  • ከተቋሙ/ ከዩኒቨርሲቲዉ ሥራ ክፍሎች ጋር የአንድነትና የመደጋገፍ መንፈስ እንዲጎለብት በተለያዩ የኮሚቴ ሥራዎች ዉስጥ በመሳተፍ የዩኒቨርሲቲዉን ተልዕኮ ማሳካት ወ.ዘ.ተ ናቸዉ፡፡

Visitors Counter

1127669
TodayToday177
YesterdayYesterday2865
This_WeekThis_Week4798
This_MonthThis_Month11542
All_DaysAll_Days1127669

 Partnerships

Oromia Health Bureau

Ethiopian Biodiversity Institute

Oromo Research and Cultural  Development Center Ethiopian Radiation Protection Authority Books for Africa